Get Adobe Flash player

በሻሸመኔ ዙሪያ ያለውን ፓለቲካዊ አለመረጋጋት ተከትሎ ቤተክርስቲያኖች እየተቃጠሉ ነው!

የአካባቢው ምንጮች ለኢትዮክርስቲያን እንደገለጹልን በጥቃቱ ጥቃት የደረሰባቸው ሽማግሌ ዎች አሮጊቶች፤ ወጣቶች ሆስፒታል ተኝተዋል፤   

ክርስቲያኖች  ሽሬ ቦረራ እሁድ የካቲት 6 ቀን  ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በጸሎት ላይ እያሉ አጥቂዎች ገብተው ከፍተኛ ጉዳት በክርስቲያኖች ላይ የተፈጠረ ሲሆን የተጎዱት ክርስቲያኖች ወደ ሻሸመኔ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን በዚህም ሽማግሌዎች ወጣቶች የቤተክርስቲያን መሪዎች ወንጌላዊያን ከተጠቂዎች ውስጥ ናቸው፡፡    በዚሁ በማግስቱ በየካቲት 7 ቀን  ሰንበቴ ሲንቂሌ 4 ቤተክርስቲያን  የካቶሊክ መካነኢየሱስ ሙሉወንጌል ቃለህይወት ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡ ይህ ስፍራ ከሻሸመኔ    50 ኪሎሜትር ያህል ይርቃል፡፡

 

ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ ጸሎትዋ እግዚአብሔር ለህዝብ ምህረት እንዲያደርግና በብዙ ዳኝነት ምድርን በሚያስተዳድረው አምላክ እጅ ላይ እራስዋን ማስቀመጥ ነው፡፡ 

“ማስተር ፕላኑ” የቤተክርስቲያን መደብደብ ምንና ምን ናቸው?

 

ለተቃውሞ ፡- አዲስ አበባው “የማስተር ፕላን ማስፋፊያ”  ተቃውሞ የአዳባ ከተማ የአዳባ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን በድንጋይ መደብደቡን መስታወቶች መሰባበራቸውን የቤተክርስቲያኒቱ አባላቶች ገለጡ ፡፡ በሌላ በኩል ለተቃውሞ ከወጡት ሰዎች የክርስቲያኖች ቤት እየተከታተሉ ማፍረሳቸው ንብረት ከማቃጠላቸው በተጨማሪ በድንጋይ ያልተመታ አንድም የክርስቲያኖች ታፔላ ያለመኖሩ ጉዳዩ ለተቃውሞ ወጥተው የነበሩ ክርስቲያን  ተማሪዎችን “ነገሩ እንዲህ ነው እንዴ” እንዲሉ አድርጎአቸዋል፡፡   የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ከዚህ ጋር እንዴት ሊያያዝ ይችላል የሚል ሲሆን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ከሚመጣ አደጋ እግዚአብሔር እንዲጠብቅ ብርቱ ጸሎት ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

 

ኢትዮክርስቲያን ለሰላም መስራት የግድ እንደሆነ ሰላም በደፈረሰ ቁጥር ሰይጣን አጋጣሚውን ተጠቅሞ የሚተኮሱ ጥቃቶችን ወደ ክርስቲያኖች ለማዞር አጋጣሚዎችን እንደሚፈልግ ከዚህ ድርጊት እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያን በሰላም እንዲባርካት ጸልየናል እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሮናል “እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በብዙ ሰላም ይባርካታል፡፡"

 

ክፉ ጠቁዋሚ ፍንጮች

 

ክፉ ጠቁዋሚ ፍንጮች

 

በሊቢያ የተፈጸመው አይሰሳዊ ድርጊት በኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ላለመፈጸሙ ምንም አይነት ማስረጃ መደርደር የማይቻሉበት ጠቁዋሚ ፍንጮች እየታዩ መሆኑን ኢትዮክርስቲያን ያምናል፡፡ መንግስት ሁኔታዎች ከሚባባሱበት መንገዶች የመግታት ሃላፊነት አለበት፡፡

ሐገራችን ኢትዮጵያ 5ኛውን ሃገራዊ ምርጫ በማከናወን ላይ በነበረችበት ወቅት ውስጥ የቱንም ያህል አሳሳቢ ዜና ቢኖርም ..ኢትዮክርስቲያን ሁኔታዎችን አድራጊዎቹ ባያፍሩበትም ስለድርጊታቸው በማፈር ለለመጻፍ ጨክነን  ነበር፡፡ ይሁንና አሳፋሪ ድርጊት እየተከናወነ ስለሆነ በተወሰነ ደረጃ መንግስት ትኩረት ሊሰጥ ስለሚገባ ዘገባውን ማውጣት አስፈልጎአል፡፡

በምስራቅ ሓረርጌ ዞን በደደር ወረዳ ቁፋንዚክ ቀበሌ መንደር  ውስጥ በአንድ ክርስቲያን ይዞታ ውስጥ መስጊድ ካልሰራን ሲሉ እቅድ የነበራቸው ሰዎች ከሶስት አመት በፊት ለመስጊድነት ባሰቡት ቦታ ላይ ያለውን ቤት ያፈርሳሉ ፡፡ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳል የደደር ፍርድ ቤት ለቀበሌው ይፈርድና ንብረትነቱ የቀበሌው እንደሆነ ይመሰክራል፡፡ ቀጥሎም ባለቤቱ ጉዳዩን ይዞ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገቡ ይሄዳል ፡፡ በዚህም የተጭበረበሩ ማስረጃዎችን ዞኑ አይቶ የደደር ወረዳ አቃቢ ህግ ወክሎ የሚሰራውን አንድ ሰው  ይህንን ማስረጃ ይዘህ እንዴት ትመጣለህ ተብሎ ተወቅሶበት ነበር፡፡ ከዚያም አቃቢ ህግ  ሌላ ሃሳብ ያውጠነጥናል ቦታው ለዩኒሰኮ የሚገባ ቦታ ነው ፡፡ ጥበቃ የሚደረግለት ታሪካዊ ቦታ ይሆናል ሲል ለዚህ ጽሁፍ አቅርቢ ተናግረው ነበር፡፡ ይሁንና ወረዳው በጫና የቦታው ባለቤት በፍቃደኝነት ለመስጊድ ማሰሪያ ሰጥቻለሁ እንዲል የሚያስማሙ ፖሊሶች ተልከው ነበር፡፡ ባለቤቱ ግን ይህንን ጫና መቀበል አልፈልግም በማለቱ ምክንያት ተይዞ እንዲታሰር በፖሊስ ሲታደን ነበር፡፡ እኛም እጅህን ለመንግስት ስጥና ጉዳዩን ብትከታተል ይሻልኃል ፤ ስንል ሃሳብ ሰጥተን ወደ ፓሊስ ለማደረስ አጠገቡ በመገኘታችን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ የአሸባሪ ታርጋ ለጥፈው ወደ እስር ቤት እንድንታሰር አድርገዋል አቶ ሚሊዮን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ፡፡ ጥር ወር 2007 ውስጥ፡፡

ከሳሶቹ  የአቃቢ ህግ ምስክር አድርጎ ያቀረበው አንዱ መስካሪ ያለው እኚህ ሰዎች ለመስጊድ በተሰጠው መሬት ላይ ቆመው አየን፤  ፎቶ ተነሱ ፊታቸው ላይ የደስታ ምልክት አለ እየተነጋገሩ ነበር ሲል መሰከረ፡፡ ቀጥሎ “ምን ድን ነው የተናገሩት” ሲል ዳኛው ጠየቁ :: አልሰማሁም ያወሩት የነበረው በአማርኛ ነው አለ፡፡ ዳኛው ውርደት የማይሰለቸው መርማሪ ፓሊስ በዚህ ወንጀል ሰው ትከሳላችሁ አሉዋቸው፡፡ ይሁንና ለተጨማሪ ቀጠሮ ሶስት ቀን ተጨመረለት ፡፡ ወረዳው አስተዳዳሪ አዘው ስለነበር ነው የተከሰስነው እንጂ እኛን ይዘው ወደ ጣቢያ የሄዱት የቀበሌው ሚሊሻዎች ሳይቀሩ እኚህ እንግዶች አላጠፉመ ጣቢያ ድረስ በመኪናችን እናድርሳችኁ ብለው ነው ለፓሊስ የመሰከሩት፡፡ ከሶስተ ቀን ተጨማሪ እስር ቀጥሎ  እኛን ሶስት ሰዎች በነጻ ተለቀን  በኋላ እንደወንጀለኛ ሲታደን የነበረውን የስፍራውን ባለቤት ተከሶ ጉዳዩ እንዲታይ አቃቢ ህጎችን አዘዙ፡፡ ወረዳው ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አብዱርሃማን(ስማቸው የተቀየረ ) ግን ይህ ሰው የራሱን ንብረት ለማስተዳደር ህገመንግሰታዊ መብቱ ሊከበርበት ይገባል፡፡ መሬቱ የሱ ነው ምን አድርጉ ትሉታላችሁ ሲሉ  ለሰውዬው ተፈረደለት፡፡ ይህም ውሳኔ በቦታ ባለቤትነቱ የዞኑም የወረዳውም ፍርድ ቤት ቢወስንለትም ..የአካባቢው ሙስሊሞች ግን ሰውዬው ጊቢ ውስጥ መስጊድ ለመስራት ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ነበር ፡፡ ይኸው መጋቢት 3 ጀምሮ መንግስት አሁን በምርጫ ስለተወጠረ መስጊዱን ሰርተን እንጨርሳለን ብለው እየሰሩ ነው፡፡ አቶ ታጁ የወረዳው አስተዳዳሪ ለዞኑ በወረዳው የፓሊስ ተወካይ ፓሊስ አብዲ ..አያሰሩ ነው ሲሉ በስፍራው የሚገኙ ሰዎች ለጽሁፉ አቅራቢ ይገልጻሉ፡፡ ፍርድ ቤት ውሳኔ በዚህ ሰዓት አቅም የለውም ቢያንስ ለዚህ ሰዓት፡፡

ጉዳዩን ለኢትዮጵያ የሓይማኖት ጉባኤ ፕሬዚደንት ፓስተር ዘርይሁን የዞን አስተዳዳሪ ለአቶ አሰግድ ወይም ለሌሎች ሪፖርት ተደርጎ መልስ ይጠበቃል፡፡ በምንም ምክንያት እነዚህ ትልልቅ ሃላፊነት ያለባቸው ሰዎች መልስ ለመስጠት ዋናና አጣዳፊውን ሃገራዊው ሰላማዊ ምርጫን መፈጸም ዋና ተቀዳሚ ስራቸው ይሆናል ..ጉዳዮች ግን አላስፈላጊ መልክ እየተፈጠረ መሆኑንን ግን ምልክት ከመስጠት አይመለሱም፡፡

የባሰው ደግሞ በአሰላ እየሆነ ያለው ነው፡፡  የዞኑ ፓሊስ ኮማንደር (ከማል)ለጽኁፉ ሳማቸው የተቀየረ …የአሰላ ከተማ  ኡስማን (የተቀየረ ስም ) እና ከጸጥታ ዘርፍ (ሙፍቲህ) የተቀየረ ስም አስተባባሪነት 7 ክርስቲያኖች ቀድሞ ሙስሊም ስለነበራችሁ በዚህ ጊቢ ምን ትሰራላችሁ በሚል በቤተክርስቲያን ገቢ ውስጥ በመገኘታቸው ለእስር ተዳርገዋል ፡፡ መጽሓፍ ቅዱሰ ሞባይ ተነጥቀዋል 18 ለቀን ታስረዋል፡፡ አሁንም ዳኛው የሚያሳስር ወንጀል የሚያደርግ የተላለፉት ህግ ስለሌለ ፍርድ ቤቱ በቀጠሮ የለቀቀ ሲሆን ታሳሪዎቹ ዋስ ጠርተው ተለቀዋል፡፡  የክርስቲያኖቹን መታሰር አመቻቾቹ  አስተዳዳሪዎች ከሆኑና አስተዳዳሪዎቹ ለፍርድ ቤት የሚያበቃ ማስረጃ የለለው ድርጊትን ወንጀል የሚያደርጉ ከሆነ ክርስትናን በማሳደድ ጉዳይ ስልጣናቸውን እየተጠቀሙ ነው ለማለት እንገደዳለን፡፡

ከዚህ ሁሉ የባስው ግን ስሙን ለጥንቃቄ ስንል የተቀየረ   ታሳሪ የደረሰበት ነው መግለጽ ይኖርብናል ፡፡   መንግስትም የሚመለከተው ሰው ሁሉ ጥበቃ እንዲያደርግለት ክርስቲያኖች እንዲጸልዩለት ያስፈልጋል ይህ ወንድም ከእስር ከተፈታ ከ ግንቦት 4   ግንቦት 9 ቀን ወደ ቤቱ ሲሄድ አመሻሹ ላይ ያደፈጡ ሽጉጥ የታጠቁ ፊታቸውን የሸፈኑ ሰዎች አፉ ላይ ሽጉ ጥ ወድረው እንዲንበረከክ ያዙታል፡፡ ቀጥሎም በሶስት ወር ውስጥ የሚፈጸም ግዴታ ያዙታል፡፡ ግዴታውም ፓስተር ግርማ ሄርጳንና ሌላ አንድ አገልጋይ እንዲገድልና ወደ እነርሱ እንዲሸሽ እነርሱም ከኢትዮጵያ እንደሚያስወጡት ቃል ይገቡለታል ይህንን አላደርገም ከለ ደግሞ ሶስቱን ልጆቹን አንድ ጉድጉዋድ እንደሚቀብሩ ዝተው እንደሚጠባበቁት ነግረውኛል ይላል፡፡  ይህ የተደራጀ ጉዳይ መኖሩን የሚያሳይ ሲሆን እንደማሳያ የሚሆን ደግሞ ከታሰሩት 7 ሰዎች ውስጥ አንደኛው ከአሰላ ተፈትቶ ወደ ወረዳው እንደደረሰ ወረዳውም ይዞ ያሰረውና ከአንድ ቀን በሁዋላ የወጣ መሆኑ…የመንግስትን ተቁዋም ለሌላ ተግባር የመጠቀም አደገኛ አዝማሚያ እንዳይኖር የሚያሰጋ ጉዳይ ይፈጥራል፡፡ ይህ ጉዳይ አሁንም  መቆም አለበት እንላለን፡፡ ቤተክርስቲያንም ለሚለከተቻው የፌደራል ፓለሲና ለሚመለከታቸው አካላት በማመልከት እየሰሩ ሲሆን እንዲህ አይነት አዝማሚያዎችን ተከታትሎ ወደ መጥፎ ጎዳና ከመሄዳቸው በፊት ለህግ አካላት ጥንቃቄ የታከለበት መረጃ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

ወርልድዋች ሞኒተር በዚህ ድርጊት ላይ ዘገባ ሰርቶበታል ኢትዮጵያም ለክርስቲያኖች አደጋ እየሆነች ካሉት ሃገሮች ላይ 22ተኛ ላይ አስቀምጦአታል፡፡ ምንጭ ፡  Nervous wait for Ethiopian Christians after baptism arrests.htm

መስከረም 26 ወንጌላዊያን ክርስቲያኖችን የጨፈጨፉ 12 ወንጀለኞች ለሁለተኛ ቀጠሮ ፍርድ ይቀርባሉ!

በጉዳቱ አንድ ሰው ሞተ ብለው ጥለውት የነበረው የቤቱ ባለቤት አቶ በዛብህ  ሲርካሶ ና  7  ወገባቸው የተሽመደመደ እጃቸው የተሰበረ በሞት አፋፍ ላይ የነበሩት  በወረዳው አንቡላንስ ሆሳእና  ሆስፒታል  ተወስደው ታክመዋል ፡፡ ሌሎች 10 በቀላል ህክምና ወደ ቤታቸው መግባት ችለው ነበር፡፡አጥፊዎቹ 40 መጽሃፍ ቅዱስ ቀደዋል ፡፡ ጥፋተኞቹ ከሶስት ወራት በሁዋላ ለፍርድ ቤት መስከረም ወር ውስጥ ቀርበዋል ፡፡

በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ተሳከ ቀበሌ እንሀናን ቁስ  ሰኔ 13 ቀን ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች አመቱን በመምህርነተ ሲሰሩ የቆየ መንግስት ሰራተኞች ወደ የ ቤተሰቦቻቸው ከመሄዳቸው በፊት ያደረጉትን የምስጋና ጊዜ ላይ ነው  የኦርቶዶክስ እምነትን በስተቀር ሌላ እምነት መኖር የለበትም ብለው የሚያምኑ ከአራት ቀበሌ የተውጣጡ ወጣቶች ቁጥራቸው ከ 100-150 የሚገመቱ ሰዎች ጩኸታቸውን ፈርተው ከውስጥ ቤቱን ዘግተ ውቢጸልዩም በገሶና በመጥረቢያ ቤቱን ሰብረው ገብተው እጃቸው የቻለውን ሁሉ አድርገው ሲጨርሱ ቤቱ ውስጥ የሚገኘውን ዕቃዎችን ሁሉ ሰባብረው እያጉዋሩ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

የአካባቢው ወንጌላዊ ክርስቲያኖች ሲገልጹ ይህንን አይነት ድርጊት ሰከናወን አራተኛ ጊዜ ሲሆን በዚህ በሰለጠነ ዘመን የእምነት ነጻነት ህገመንግስታዊ ጥበቃ በሚደረግበት ወቅት  በእንደዚህ አይነት ዘመቻ መውጣት አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ መንግስት የሰጠንን መሬት ነጥቀውናል ድጋሚ ሲሰጥ አጥሩን አደቃጥለዋል በመጨረሻም በአነስተኛና በጥቃቅን ተደራጅተው ቦታውን በጉልበት ይይዘውታል፡፡   የወረዳው ባለስልጣኖች አጥፊዎቹ ለህግ ለማቅረብ  የማግባባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉት የተጎጂዎቹ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ይገልጻሉ!

ይህ ድርጊት ወንጌላዊያን ክርስቲያኖችን በእንዲህ አይነት ሁኔታ ማጥቃት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም አስተምህሮ ስላይደለ እንዚህ አጥፊዎች ቅጣታቸውን ተቀብለው ሌላውን እያከበሩ ቢየስፈልግ በመልካም ስራ ምሳሌነታቸውን በማሳየት በከርስቶስ ፍቅር ሰዎችን እንዲማርኩ ይጠበቃል! 

የዶዶላ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ “የድምጻችን ይሰማ” የሚል ወረቀት በመበተን ተጠርጥሮ ታስሮ ተፈታ

 

አለማየሁ ለገሰ የዶዶላ መጽኃፍ ቅዱስ ተማሪ የነበረው እስልምናን በክርሰትና አተያይ የሚያብራራ ጽሁፍ ፎቶ ኮፒ ሲያደርግ ተገኘ ተብሎ ያለፍርድ ለሶስት ወራት ታስሮ በዋስ የተፈታ ሲሆን ፤ ለአመታት ያህል ፍርድ ቤት በመመላለስ አቃቢ ህግ ምስክር ማቅረብ አቅቶት በመመላለስ ላይ ያለው ሰው  ህዳር 25 ደግሞ አባረው ቤት ሰብረው ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ወንበዴ እንደሚይዝ ሃይል አስጠርተው ቤቱን ከበው፤  በመጨረሻ   ይዘውት ወደ ጣቢያ ወስደው ዋስ አስጠርተው  ተለቋል፡፡

አለማየሁ ለምን እንደታሰረ ሲጠይቅ “ለሊት የተበተነ ወረቀት ተጠርጥረህ ነው  “ጩኸታችን ይሰማ” የሚል የተጻፈ መፈክር አለ ይህንን ያለላንተ የሚሰራው የለም”  በማለት ነው ወስደውኝ የነበረው እና ግራ ገብቶኛል ሲል ገልጿል፡፡

 3/4 ኛው ሙስሊም የሆኑት የዶዶላ ፓሊሶች “ድምጻችን ይሰማ” የሚለውን ታዋቂ ድምጽ የየት የቱ እንደሆነ ሳያውቅ ወደ ቤተክርስቲያን ማተኮሩ ወደት ሊያመራ እንደሚችል መጠርጠር ይገባል ይላሉ በስፍራው ያነጋገርኩዋቸው፡፡

 

Facebook Like Button